ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #196d / Song #196d

ርስትህን ለማላገጫ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
1.
በደልን ይቅር የሚል አመጻን የሚያሳልፍ
ከጥፋት ሊያድናቸው በርስቱ ላይ የሚፈርድ
እንዳንተ ያለ አምላክ ማን ነው ምህረቱ የበዛ
ቅዱሳን ሲሰደዱ መከራም ሲበዛ
ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ
የተቀደሰ መቅደስህን በጠላት አታስረግጥ
2.
የእግዚአብሔር ዕድል ፈንታ ተጽፏል ህዝቡ ነው
ሊሚያመልከው ሊያገለግለው ከግብጽ አገር ያፈለሰው
አርነቱን በባርነት ሊተካ የሚከጅለው
ይገባኛል የሚል ማን ነው? ርስቱ የእግዚአብሔር ነው
3.
እስከዛሬ ከብረሃል በአህዛብ ተፈርተሃል
የጠላትን እርግማን በረከት አድርገሃል
የአሳዳጆችን ፈረሶች በባሕር አስጥመሃል
በክንድህ ተከላክለህ ርስትህን ጠብቀሃል
100%
100%