እኔን ጌታ ሆይ ድካም ይዞኛል
ድምጼንም ላሰማህ አቅቶኛል
ወድቄአለሁኝ ጌታ ሆይ አንሳኝ
እባክህ ሕይወቴን ለውጥልኝ
1.
ቃልህን ለማንበብ ዐይኔ ታወረ
ሳልጸልይ ጉልበቴ ታሰረ
አንተን እንዳላስብ አዕምሮዬ ዛለ
እግሬም ወደ ጥፋት ኮበለለ
2.
ጠፋሁኝ ጌታ ካልደረስክልኝ
ዓለም እንደ ጐርፍ እንከባለለኝ
በኀጢአት ባሕር ልሰጥም ነውና
ጌታ ሆይ እባክህ እጄን ያዘኝ
3.
አየሁ ጌታዬን ወዲህ ሲመጣ
እኔን ከጥፋት ሊያወጣ
እጁን ላከልኝ ፍፁም አዳነኝ
ከእንግዲህስ ከጌታዬ ጋር ነኝ