ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #134 / Song #134

በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ
በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ
በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ
ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ
መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ
1.
በግብጻውያን በደል በዓመጻቸው
ቁጣህ ከላይ ወርዶ ሲፈጃቸው
ደምህ ተቀብቶ በመቃኔ
ምክንያት ሆኖልኛል ለመዳኔ
ተጠነቀክልኝ እንዳልጠፋ
ዙፋንህ ከፍ ይበል ይንሰራፋ
2.
በኮሬብ ተራራ በእሳት አምሳል
ለነብዩ ሙሴ ተገልፀሃል
በእኔም ልብ አንድደህ የፍቅር እሳት
ምስኪኑን ሕይወቴን ስታጋያት አይቻለሁ እና እንዳቅሜ
አመሰግናለው ይኸው ቆሜ
3.
ከኃጤአቴ በቀር ከመርከሴ
የማውቀው የለኝም ስለራሴ
አንተን ግን አውቃለሁ ስታድንኝ
የድሃ አደግ አባት ስትሆነኝ
በፍቅር ይዘኸኛል በውዴታ
እኔም ላመስግንህ በእልልታ
4.
አጋጣሚ አይደለም ያገናኘን
እንደ አባት እና ልጅ ያቆራኘን
ለእኔ ያሰብከው ያኔ ድሮ
ዛሬ ተፈፀመ ዘመን ቆጥሮ
ያረካህ እንደሆን ይኸው መልሴ
ምስጋና እና ክብር ከውዳሴ
5.
1.በስሙ ለሚያምኑበት ለሚቀበሉት
የእግዚአብሔርን ልጅነት ስልጣን ለመስጠት
ከሰማይ ሁሉ በታች የሚዳንበት
ከቶ ሌላ ስም የለም ለሰው ደህንነት
የጌታ ስሙ ብቻ ነው
6.
ስሙ ኃይል አለው የጌታ (3x)
7.
2.አንተ ምስኪን ሽባ ሰው መሄድ ያቃተህ
ብርና ወርቅ የለኝም ላንተ የምሰጥህ
ነገር ግን በኢየሱስ ስም ተነሳ ድነህ
ሲለው ሽባው የዳነው መዝለል የቻለው
ኃይል ባለው በኢየሱስ ስም ነው
8.
3.መልካም ስጦታ ከላይ የሚገኝበት
ልመና በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርብበት
በስሜ ለምኑ የሚል ተስፋ ያለበት
ከቶ ሌላ ስም የለም ከጸሐይ በታች
የኢየሱስ ስሙ ብቻ ነው
9.
4.ከብዙ ኃያላኖች ብዙ ስም በላይ
ከብዙ ታዋቂዎች ብዙ ስም በላይ
ከስሞች ሁሉ በላይ ታላቅ ስም ያለው
መዳን በስሙ ለሰው ሁሉ የሰጠው
ኢየሱስ ጌታ ብቻ ነው
100%
100%