ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #102d / Song #102d

ተስፋ ቆርጩ በእንባ ሳለሁ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ደረጀ ከበደ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
አንዳንዴ ፈተና ሲያጠቃቃኝ
እምነቴም ሲጠፋ የሰጠኸኝ
ባላሰብኩት ሰዓት ድምፅህ መጥቶ
ንቃ አይዞህ ይለኛል ተጠግቶ።
ተስፋ ቆርጩ በእንባ ሳለሁ
ያንተን ድምፅ ስሰማ እነቃለሁ
አይዞህ ባይ ነህና ደካማ አጽናኝ
የፈረሰን እምነት ጠጋኝ
2.
ከጠላት ስዋጋ ክንዴ ዝሎ
ጦሬ ከእጄ ሲወድቅ ኃይሌ ወድሞ
አበቃሁ እንግዲህ ወዮልኝ ስል ው
ድምፅህ ይሰማኛል አይዞህ ስትል።
3.
የረዳት ያለህ ስል በዚያን ጊዜ
መናገር አቅቶኝ ሲወርድ ወዜ
የመለያ ሰዓት ፈውስ ሞቴ
ተስፋዬ ባንተ ነው ሞት ሽረቴ።
100%
100%