1.
ነገን እኔ አላውቅም
አንተ ግን ታውቀዋለህ
ስለዚህ እጄን ይዘህ
ምራኝ ክፊቴ ቀድመህ
ለኔ የምታስበው
በጐና መልካም ነው
ፍፃሜና ተስፋ አለው
የሰላም ሐሳብ ነው አመሰግንሃለሁ።
2.
ትምህርትህ ይጠቅመኛል
ብርሃን ለመንገዴ ሆኗል
መንፈስህ ያጽናናኛል
መንገዴን ይመራኛል።
3.
ይካማ ነኝ አውቃለሁ
ራሴን ለአንተ እሰጣለሁ
እንደ ፈቃድህ ምራኝ
እንደ ሐሳብህ አኑረኝ።
4.
በጨለማ ውስጥ ባልፍም
ችግር ቢደራረብም
ሁሉም ግን ለመልካም ነው
ለጥቅሜ የምታደርገው