ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #139 / Song #139

አቤት በፀሎት እርካታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ከላይ ሲመለከት ጌታ
ሸክሜ መስቀሉ ሥር ወድቆ
የሚገዳደረኝ ደቆ 2x
1.
እግሩ ሥር በፀሎት በእምነት ቀርቤ
ተመለስኩኝ ሞገስ ፀጋውን ደርቤ
ተዘጋጅቶ የቀረበው ታላቅ ባርኮት
ቀረብኩና ተቀበልኩት ከፀባኦት
2.
ምርኮዬን ዳግመኛ ጌታ መለሰልኝ
በመንፈሱ እንደገና ሕይወት ሰጠኝ
ተሸክሜ የመጣሁት የከበደኝ
የኔ ጌታ ሸክሜን ሁሉ ወሰደልኝ
3.
እንባዬን አፍስሼ ብሶቴን ነገርኩት
እኔም ሳለቅስ እርሱም ሲያለቅስ ተጠጋሁት
አይዞህ ልጄ በደል ሁሉ ተወግዷል
ብሎ ሲለኝ በደል ሁሉ ተንከባሏል
4.
ደግመኛ ሸልሞ በደስታ ሞላኝ
በሩቅ ያሉት መጐብኘቴን ተረዱልኝ
ሳይሰለቸኝ እንደገና ስላነሣኝ
እጥፍ ድርብ ለዚህ ጌታ ቅኔ ልቀኝ
100%
100%