በእርግጥ ጌታ ከኛ ጋር ባይሆን
እርሱ ባይዋጋልን
የጠላታችን ሠልፍ አይሎ
ከምድር ላይ በጠፋን
ስለዚህ ስለዚህ
እግዚአብሔር ይመስገን
ስለ ሁሉም ነገር
1.
የእሣት ሠረገላ ብዙ ሠልፍ ከቦናል
ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉም ይበልጣል
መለከትን ንፉ ጠላት ይታወራል
ብቻ ዕምነት ይኑረን ኢየሱስ ያሸንፋል
2.
በብዙም በጥቂት ማዳን ላይሳነው
ኤረ ለመሆን የሚነካን ማን ነው?
ቀድሞስ በባዕድ ግዛት መቆየት መች አሻን?
ይህስ ባይሆን ወንዙን ስለምን ተሻገርን?
3.
አለችን ውብ አገር ኗሪ ከተማ
በውስጧ የዕሮሮ ድምፅ የማይሰማ
እንጋደላለን እስክንጨብጣት
አምላክ ይረዳናል በምንደክምበት
4.
የአማሌቅ ተቃውሞ የፈርዖን ሠልፉ
በሠራዊት ጌታ እንድናይ ሲረግፉ
ድምፃችንን እናንሳ መለከትን ንፉ
የዕምነትን ጥሩር በራሣችሁ ድፉ