ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #152 / Song #152

ኮብልላ ነበረች ነፍሴ ከእግዜር መንገድ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ኮብልላ ነበረች ነፍሴ ከእግዜር መንገድ
በጣም የበደልኩኝ ኃጢያተኛም ነበርኩ
ግን አዳኜ ከላይ ፍቅር ሠጠኝ ሠላም
ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
1.
ደሙን ለኔ አፍስሶ አዳነኝ/2X/
የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ
ልጁን ለኔ ልኮ አወጣኝ
2.
ተስፋ ቢስ ነበርኩኝ ሊያወጣኝ ሲመጣ
ግን እርሱ ነገረኝ ነፃ እንደምወጣ
ከዚያም አነሳና ክብሩን አቀዳጀኝ
ልጁን ለኔ ልኮ አወጣኝ
3.
ልቤን ደስ ይለዋል ከመረጥኩት ወዲህ
ከማዕበሉ አሁን ወደ እርሱ እጠጋለሁ
ክንዱን ከተደገፍኩ አልፈራም መከራ
ጌታ ለኔ ወርዶ አወጣኝ
4.
ሠማያዊ ደስታ ሠላምን ከሠጠኝ
ጌታ ሆይ ሕይወቴን ለአንተ እሰጣለሁኝ
ከእንግዲህ እጄን ያዝ ከአንተም ጋር አቆመኝ
ልጁን ለኔ ልኮ አወጣኝ
100%
100%