እንመሠክራለን ማዳኑን
እንናገራለን ትንሣኤውን
ለኛ ሲል በመስቀል የሞተውን
የናዝሬቱ ኢየሱስ አዳኙን
1.
ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን
ከዘላአለም ሞት ያወጣንን
ሕይወት አግኝተናል በየሱስ ሞት
እንመሠክራለን በድፍረት
2.
ቀንበራችንን ሁሉ ሠባብሮ
መንገዳችንን ሁሉ አሳምሮ
የቀድሞው ሥማችንን ቀይሮ
እንደገና አቆመን ዘንድሮ
3.
ከፊት ለፊታችን ተራራ
ከጐናችን ደግሞ መከራ
በሞት አዋጅ ዙሪያችን ተከበን
የናዝሬቱ ኢየሱስ አወጣን
4.
በምድርና በሠማይ መኸከል
ሰለኃጢአታችን በመንጠልጠል
በቀራኒዮ ፍቅሩን ገልጾልናል
መዳናችን ያኔ ተረጋግጧል