1.
ዛሬ የምናየው ነገ ጠፊ ነው
ዛሬ የምንሰማው ነገ የሚቆር ነው
በዓለም ሚታየው ሁሉ አይኖርም
ጌታችን ብቻ ያው ነው ዘለዓለም ።
እኛ የምናምነው ግዑዝ አይዶለም
በየምክንያቱ መልኩ አይቀየርም
ያው ነው አሁንም ያው ነው ዘለዓለም
አልፋ ኦሜጋ ሕያው ነው በዓለም።
2.
በጽኑ ድንጋይ የተገነባው
በዓይን ሲታይ ፈራሽ የማይመስለው
የምንኖርበት የዚህ ምድር ቤት
እርሱም ይፈርሳል ቀን ሲደርስለት።
3.
እስኪ አስቡ ለትንሽ ሰዓት
በጣም ጠንካራ አለ የምትሉት
እርሱም ይቀልጣል ሲፈተን በእሳት
የማይቀር የለም በዚህ ዓለም።
4.
ተወዳዳሪ ያልተገኘለት
ልዑል እግዚአብሔር የእኛ አባት
ልዩ ነውና አቻ የሌለው
ቅዱሳን ሁሉ ኑ እናክብረው።
5.
ከጥንት ነበርህ ምድርን መሥርተህ
ሰማያትንም በጅህ ዘረጋህ
ደግሞ እነዚህም ሁሉ ያረጃሉ
አንተ ግን አንተ ነህ በዘመን ሁሉ።
6.
የማይፈርሰውን የማያረጀውን
እኔ መርጫለሁ ያው እግዚአብሔርን
በምድር የሚታየው ሁሉ ይቀራል
እርሱ ብቻውን ጸንቶ ይኖራል ።