ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #304d / Song #304d

ጌታ ኢየሱስ ሆይ እጄን ያዘኝ

English Translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
ጌታ ኢየሱስ ሆይ እጄን ያዘኝ
የማልረባ ነኝ ኃይል የሌለኝ
1.
የማደርገው ሲገባኝ ግራ
ኑሮ ሲሆንብኝ መራራ
የምታጣፍጥ ጨው ቅመሜ
ርቀህ አትቁም ከአጠገቤ
2.
እኔ የያዝኩ እንደሁ እጅህን
መከተል ሲያቅተኝ እርምጃህን
ድንገት እለቅሃለሁ ደካማ ነኝ
አንተ አትደክምም እጄን ያዘኝ
3.
በጨለማው አለም ስመላለስ
ተሰነካክዬ እንዳላለቅስ
መንገዴን አሳየኝ ብርሃን ሆነህ
ጺዮን አግባኝ እጄን ይዘህ
4.
ሥጋ ለባሹ ሳይ ባይኖቼ
ሰውን ይዤ ስሮጥ በእጆቼ
የተሰባበርኩት ቁስሌ አልሻረም
አንተው ይዘኝ ለዘላለም
100%
100%