1.
ምቾት ሲበዛ ጸሎት ሲረሳ
የአምልኮ መንፈስ ከእኔ ሲነሳ
ሲበዘበዝ ቤቴ ስዘረፍ
ኧረ ምንድነው የእኔ እንቅልፍ
አሁንስ ልነሳ ልንበርከክ ልፀልይ
በቃሉ ብርሃን እስኪ ጏዳየን ልይ
ምሽጌን ልጠብቅ መንገዴን ልሰልል
ወገቤን ልታጠቅ በጉዞየ እንዳልዝል
2.
ሌሊቱን ሁሉ ሲሞቀኝ አልጋ
አንድም ሳልጸልይ በእንቅልፍ ሳነጋ
መቼ ታወቀኝ እንዲህ መሆኑ
ገና ይመስላል አልቆ ዘመኑ
3.
የአለምን ክፋት ንቄው ለማለፍ
በጠላት ውጊያ ላለመሸነፍ
ኧረ ልስጠው እጄን ለጌታ
አያዋጣኝም ይሄ መኝታ
4.
ሲቀሰቅሰኝ የአምላኬ መንፈስ
በፍቅሩ ሃይል ነፍሴ እንዲታደስ
እኔም ልንቃና ጌታን ላምልከው
ልትጋ ልፀልይ ቃሉን ላንብበው