ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #330d / Song #330d

እንደ ሎጥ እንደ ኖህ ዘመን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
እንደ ሎጥ እንደ ኖህ ዘመን
ሀጢያትን እጅግ አበዛን
ጌታ ሆይ እባክህ ገስፀን
አባት ነህን ቆንጥጠን
ስንጠፋ ዝም አትበለን (2)
1.
ልባችንን የመንፈስህ ማደሪያ
ሀጢያት አሻገተው
መቅደስህን ተነስ ጌታ ሆይ አፅዳው
ስጋችንን ግታው
2.
ደግመህ ደግመህ ስቀለው ስጋችንን
እንምሰልህ አንተን
በመንፈስህ የጀመርነው ጉዟችን
ለሕይወት ይሁንልን
3.
ቅዱስ ስምህን አረግነው መነገጃ
ብር ወርቅን ማትረፊያ
መኖራችን ነበረ ለአለም ብርሃን
ጨለማ ሆነናል
4.
በሰናኦር ግንባችንን ሰርተናል
እጅግ ተኩራርተናል
ሀጢያት ለብሰን አመፃን ደርበናል
ፈውስ ይስፈልገናል
100%
100%