ጌታ ያደረገው ለኔ የሠራልኝ ስራ
አያልቅም ቢነገር ቢተረክ ቢወራ
የየሱሴ ስራ
1.
ለብዙ ዘመናት አንገት ያስደፋኝን
ከተፅእኖ በታች እኔን ያረገኝን
መርገሜን ከኔ ላይ ወሰደው
የእዳ ጽህፈቴን ደመሰሰው
ዳግመኛ ጠላቴ ላይከሰኝ
አምላኬ ፈይሉን ቀደደልኝ
በነጻነት ኖራለሁ ሳልሰጋ
ኢየሱስ ስላለ ሁሌ ካኔ ጋር
2.
መስሎት የተረሳሁ አስተዋሽ የሌለኝ
በጽኑ ባርነት ሊያስገባኝ
ቀንበሩን በኔ ልጭንብኝ
ሌት ቀን ሳይደክም ስተጋ
አምላኬ ጭንቅላቱን ወጋው
ከመሬት ጋር አጋጨው አደበላላቀው
መታሰቢያውን ከሙታን መንደር አረገው
3.
ዛሬ በነጻነት ደስ ደስ እያለኝ
ዘምራለሁ ለርሱ ረዳት ስለሆነኝ
ያጎበጠኝ ወንበር ተሰብሯል
መፈታፍ በእኔ ታውጇል
ባሪነት ተሽሯል
ዲያብሎስ ባዶ እጁን ቀርቷል
አምልጫለሁ አምላኬ ጉልበት ሆኖኛል
የጠላቴን መንጋጋ ሰባብሮልኝ