ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #186d / Song #186d

በረከትና ክብርም ጥበብም

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
በረከትና ክብርም ጥበብም
ባለጸግነት ኃይልም ብርታትም
በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው
ለነበረው ላለው ለሚመለሰው
ለታረደው በግ ምሥጋና ይድረሰው (4x)
ራዕ 5፡9-10
1.
መጽሐፉን ወስዶ ማኅተሙን ፈትቶ
ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅቶ
ለአምላክ መንግሥት ካህናት ሆንን
በበጉም ስራ ተመሰገንን
ራዕ 5፡13
2.
በሰማይ በምድርም ከምድርም በታች
በእነርሱም ውስጥ ያለን ፍጥረታት
ከዙፋኑ ፊት እንወድቃለን
ለበጉም ክብር እንዘምራለን
ራዕ 5፡11-12
3.
እልፍ አእላፋት ብዙ መላእክት
ለታረደው በግ እሚሰግዱለት
እስከዘለዓለም ለሚኖር ጌታ
ቅኔ ሲቀኙ ጥዋትም ማታ
ራዕ 7፡13-17
4.
ከታላቅ መከራ የመጡ ናቸው
በበጉ ደምም አነጹ ልብሳቸውን
በዙፋኑ ፊት ሌት ተቀን አሉ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ
100%
100%