ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #222d / Song #222d

ደመናም የለም የጠራ ሰማይ ነው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ብዙ ደከምኩኝ አልተሳካም
ብዙም እሮጥኩኝ ግን አልሆነም
አንተ ግን ጌታ አላማ አለህ
ሁሉን በጊዜው ታደርጋለህ (፪x)
ደመናም የለም የጠራ ሠማይ ነው
ነፋስም የለም ምልክት የማየው
አንተ ግን ጌታ ሁሉን ትችላለህ
ዝናብን ከላይ ታዘንባለህ
አንተ ግን ኢየሱስ ሁሉን ትችላለህ
ሸለቆውን ውኃ ትሞላለህ
2.
አምናለሁ ጌታ አትረሳኝም
የልቤ መሻት ቢዘገይም
በአንተስ ጌታ ሆይ ተስፋ አልቆርጥም
ቃልህን እንደ ሰው አትለውጥም (፪x)
3.
በአንተ ማረፉ ይበጀኛል
በከንቱ ብደክም ምን ይገኛል
አንተን ልጠብቅህ ይሻለኛል
የእኔውስ መንገድ ያጠፋኛል (፪x)
100%
100%