ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #240d / Song #240d

ጌታ ለኛ ያደረገው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 6
1.
የማይቻለው በእርሱ ተችሎ
ሲዝት ሲፎክር ስንቱ ተጥሎ
በሚያበረታው ጌታ በርትተን
እዚህ ደርሰናል ሁሉንም አልፈን
ጌታ ለኛ ያደረገው እጅግ ብዙ ነው
አቤት ስንቱን አልፈን በእርሱ ችለነው
ብርታት ጉልበት ሆነልን
ስሙ ከፍ ይበልልን
2.
ባሕር ሞገዱን በስልጣን አዝዞ
በፍቅር እጁ እጃችንን ይዞ
ከዘመን ዘመን አሸጋግሮናል
ክብር ለስሙ ይሁን ብለናል
3.
ብቸኞች መስለን ረዳት የሌለን
ስንቱ ሲቃጣ ይዞ ሊያስርቀን
የነአብርሃም የይስሓቅ አምላክ
በድል መርቶናል ስሙ ይባረክ
4.
ስንቱ ታለፈ ተረግጦ በእግር
ላያንሰራራ ዳግመኛ ላይኖር
የአንበሳውን መንጋጋ ዘግቶ
አቆመን ጌታ ፀጋውን ሞልቶ
100%
100%