ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #306d / Song #306d

ውለታው እጅግ ብዙ ነው

English translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
ውለታው እጅግ ብዙ ነው
አልችልም በቃል ልገልጸው
ተመስገን ብቻ ልበለው
1.
ከቀራንዮ ሞት ጀምሮ እኔን እንከሞት አፍቅሮ
ነፍሴን በነፍሱ ለውጦ ደሙን በእንባ ቀይጦ
እኔን ልያበለፅግ ደህይቶ ነፍሱን ከስጋው ለይቶ
ንጹህ የደም ላብ ያላበው ይህ ሁሉ ድካም ለእኔ ነው
2.
ይከሰኝ የነበር ባለፈው ጠላት በግንባሬ የጻፈው
የእዳዬን ጽህፈት ደምስሶ ዝገቴን አጥቦ አንፅቶ
ሰው አደረገኝ ረድኤቴ ሰላሙን ሞላው በቤቴ
የከሳሼ ግንባር ተመታ እኔም ዘምራለሁ በደስታ
3.
ድካሜ ብዙ ነው ጉለቴ በፀጋው ነው አለሁ ማለቴ
በድፍረት ሥሙን መጥራቴ ጌታ የሰራውን ማውራቴ
ሰው ሆኜ በምድር መኖሬ በሰላም ውዬ ማደሬ
እግሬም ጸንቶ ሊቆም የቻለው ይህ ሁሉ በእርሱ ጸጋ ነው
100%
100%