ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #146d / Song #146d

እንጸናለን በጊዜው አለጊዜውም

English Translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
እንጸናለን በጊዜው አለጊዜውም
ዛሬ የጠበቀን ነገም አይተወንም
እንጸናለን
1.
ወደ እሳት ልንጣል ልንቃጠል
ዓይናችን እያየ ስንበለበል
እውነትስ ጌታችን ወዲያ ካለን
ለጅራፍ ጀርባችን እንሰጣለን
2.
አባቶችን በእምነት ያቆመውን
በመጋዝ መሰንጠቅ ያጸናውን
ያ አምላካችን ነው አምላካችን
የሚያጸና ጉልበት ታዳጊያችን
3.
የከንቱ ቃላቶችን ደርዳሪ
አንሆንም በስጋችን ፎካሪ
መንፈሰ ያስቻለንን ልንቀበል
ተሸክመን አለን የእምነት ቀንበር
4.
ሲድራቅና ሚሳቅ አብድናጎን
ካቶን እረመጥ ውስት ያወጣውን
የሕዝቡን ጠላቶች የሚበቀል
ዛሬም ከእኛ ጋር ነው የእግዚአብሔር ኃይል
100%
100%