ክብር ይገባሃል የእኛ አምላክ (2)
ዙፋንም ምሥጋናም ለአንተ ነው (2)
ክብር ሃሌሉያ (3) ክብር ሃሌሉያ
1.
እግዚአብሔር ነገሠ ክብር ለበሰ
ታጠቀ ኃይልንም ለበሰ
ዓለምን አጸናት አቆማት
ምሕረቱም ድንቅ ዘለዓለማዊ
2.
ዘለዓለማዊ አምላክ አንተ ነህ
ዝግጁ ነው ከጥንት ዙፋንህ
ወንዞች ከፍ አደረጉ ድምጻቸውን
ተራሮች ጨሱ፡ ሰጡህ ክብርን
3.
ከብዙ ውሃዎች ድምጽ ይልቅ
ከታላቅ ሞገድም ድምጽ ይልቅ
ጌታችን አንተ ነህ ኃያል ድንቅ
ምስክር ታማኝ አንተ ታላቅ