በትዕግሥት ጸጥታ በጸሎት ቆይታ
ድል ይገኛል ከጌታ
በትዕግሥት ጸጥታ በጸሎት ቆይታ
መልስ ይመጣል ከጌታ
1.
የበረታ ሰልፍ ሲከበኝ ከኋላ ከፊት
ቆይቼ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት
እርሱም ዘንበል አለልኝ ሊያዳምጠኝ
እንባዬን በእጁ ጠርጐ ቃሉን ሰጥቶ አጽናናኝ
2.
ነፍሽ ስትራቆት ፍፁም ባዶ ስትሆን
ያለህን አራግፈህ ዘርተህ ስታይ ራስህን
ያሳለፍካቸውን ድሎች አስብ ተስፋህ ይለምልም
ተንበርክከህ ብትቆይ ደግሞ መዳሰሽ አይቀርም
3.
ከድካም የበረቱ ሰዎች በድል ያለፉ
ከኢየሱስ በስተቀኝ በላይ የተሰለፉ
መንግሥታትን ድል ነስተው ያኔ ምሽግ የናዱ
የጸሎት ሰዎች ናቸው ጠላት ያርበደበዱ