ቀሪ ዘመኔን ጌታ ባርከው
ምን ያህል ይሆናል?
ባለፈውማ ብዙ ነገር
ሥጋዬ አበላሽቷል
1.
ጉልበቴ በባዕድ ምድር ጣዖትን አክብሯል
የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ሥጋዬ አበላሽቷል
ዓይኖቼ ወዳዩት ሁሉ እግሮቼ ሮጠዋል
ያለፈው ዘመኔ ሲታይ እጅግ ያሳዝናል
2.
አርነቴን ተከልዬ ብዙ ቀልጃለሁ
ፀጋህ ለእኔ ስለበዛ ሳውቅም በድያለሁ
አቤት! ምን ያህል ታጋሽ ነህ ከበደሌ በላይ?
እባክህ የቀረኝ ዘመን ፊትህ ከብሮ ይታይ
3.
በተቀደሰው መቅደስህ ደምን አፍስሻለሁ
አንተ የምትተክላትን ነፍስ እኔ ገድያለሁ
ዓለም በአንተ ላይ ስትተፋ ተባብሬያለሁ
ጌታ ባለፈው ዘመኔ ብዙ ባክኛለሁ