የእኛ ጌታ የእኛ ኢየሱስ
ትላንትናም ዛሬም አዲስ
ሥሙ ኃያል ነው የሚፈውስ
1.
ትላንት የነበረው ታላቅ ኃይሉ
ዛሬም ይሠራል በዓለም ሁሉ
እንመካለን በጌታችን
ሲሰራ አይተናል በዓይናችን
2.
የጠላትን በር ጥሶ ገብቶ
የሕይወትን ቃል በእኛ ዘርቶ
አዲስ አደረገን እንደራሱ
ክብር ይሁንለት ለንጉሡ
3.
ሁልጊዜ አዲስ ነው የማይሻር
ክንዱም ጠንካራ የማይበገር
የሆነው ኢየሱስ የእኛ ጌታ
ታላቅ አምላክ ነው የማይረታ
4.
የድሉ ጌታ ጌታችን ነው
እናምነዋለን ስሙም ይኸው
ላንክደው ቃል ገብተናል
አንዋሽም ክንዱን አይተናል