ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #41h / Song #41h

ጌታ አምላኬ

How Great Thou Art

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ጌታ አምላኬ እንዴት እገረማለሁ
ሳስብ ሳለሁ የጆችህን ፍጥረት
ከዋክብትን ሳይ ነጐድጓድን ስሰማ
ያንተ ሥልጣን በሕዋህ ውስጥ ታየኝ
ነፍሴ ላንተ
መዝሙር ታቀርባለች
ኃያል ግሩም ታላቅ አምላክ
ነፍሴ ላንተ መዝሙር ታቀርባለች
ኃያል ግሩም ታላቅ አምላክ
2.
ጥቅጥቅ ባለው
በደን ውስጥ ስመላለስ
የወፎችን ዝማሬ ስሰማ
ሳይ ወደ ታች ከፍ
ካለው ተራራ ላይ
ምንጩ ሲፈልቅ
ነፋሱም ሽው ሲል
3.
ሳስብ ሳለሁ
አብ ለልጁ ሳይሳሳ
እንደ ላከው
ሊሞት በኔ ፈንታ
በመስቀል ላይ
ሸክሜን በደስታ ችሎ
ተሰቃየ
ኃጢአቴን ለመውሰድ
4.
ክርስቶስ የሱስ
በታላቅ ክብር መጥቶ
ይዞኝ ሲሄድ
ደስታዬ እንዴት ይሆን
ከዚያም ለርሱ
በምስጋና እሰግዳለሁ
ለታላቁ ግሩም
ኃያል አምላክ
100%
100%