ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #78d / Song #78d

ግሩም ነው ድንቅ ነው ጌታ ሲሰራ

English Translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
ግሩም ነው ድንቅ ነው ጌታ ሲሰራ
አየነው ምርኮው ላይ ግርማው ሲያበራ
የኃጢአት መጋረጃን በደሙ ቀደደ
ከሳሻችን አፍሮ ወድቆ ሰገደ
1.
ይከሰን የነበረው የእዳ ጽሕፈት
በደሙ ተደምስሷል በጌታ ኢየሱስ ሞት
ቀንበራችን ተሰብሮ አርነት ወጥተናል
ጠላቶች የነበርነው በፀጋው ቀርበናል
2.
ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን
በጌታ ኢየሱስ ሥራ እግዚአብሔር ጠራን
ተስፋችን ያከተመ ደካሞች ሳለን
በዘመኑ ፍፃሜ በልጁ ዋጀን
3.
አእላፋት መላዕክት አገልጋይ ሳያንሰው
ስለጠፋው የሰው ልጅ አንድ ልጁን ሰዋው
በኃጢአት ረግረግ ውስጥ ሰጥመን ለጠፋነው
ሊታደገን ወደደ ጭንቀታችን ተሰማው
4.
መንገድ ተዘጋጀልን ግዛቱ ልንገባ
የከበደን ቀንበር ሆኗል እንደ ገለባ
እንራመዳለን ሸክም ቀሎናልና
ዕረፍትን ስላገኘን ሆነን በምሥጋና
100%
100%