መንገዴን ሁሉ ሁሉ
ጌታ ከአንተ ጋር
እስከ መጨረሻው ልጓዝ
ልሁን ከአንተ ጋር
1.
የዘለዓለም ሕይወቴ ነህ መጠጊያና አምባዬ
እስከ ፍጻሜ እሄዳለሁ አንተን ተከትዬ
መንገዴን ሁሉ ከአንተ ጋር እስከ መጨረሻ
እከተልሃለሁኝ የሕይወቴን ጋሻ
2.
በመከራ በስደትም በሚያስፈራ ነገር
ለአንተ ፀንቼ እቆማለሁ በሕይወት እንድኖር
የልብ ሰላምንና ደስታን ከሰጠኸኝ
ለአንተ ፀንቼ እንድቆም አደራ አስበኝ
3.
የሚያሰናክለኝ የለም ከክንፍህ ሥር ነጥቆ
ማንም ሊወስደኝ አይችልም ከእጅህ ፈልቅቆ
ሰይጣንም ከአንተ ሊነጥለኝም ቢሞክርም
ከአንተ ፍቅር ፍፁም ሊለየኝ አይችልም
4.
ደስታ እንደሌለኝ አውቃለሁ ከአንተ ከተለየሁ
ነገር ግን ተስፋ የሌለኝ ከርታታ እሆናለሁ
ግን እስከ ፍጻሜው ከአንተ ጋር ከተጓዝኩ
በሰማይ የደስታ ቤት እንዳለኝ አውቃለሁ