ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #82d / Song #82d

አዬ! ብቸኛው

English Translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
አዬ! ብቸኛው አዬ! ብቸኛው
ስለ በደሌ ሲል ሆነ ብቸኛ ሰው
1.
መልክ ውበቱን አጥቶ መድኅኔ
ተዋረደ ለማልጠቅመው ለእኔ
ውለታ ዋለልኝ የማልረሳው
ትዝ የሚለኝ ከልቤ የማይጠፋው
2.
መልክ ውበቱን አጥቶ መድኅኔ
ለጠፋሁት ተዋረደ ለእኔ
ተጓዘልኝ መስቀል ተሸክሞ
ተራራውን ወጣው ለእኔ ደክሞ
3.
መልክ ውበቱን አጥቶ መድኅኔ
ተዋረደ ለማልጠቅመው ለእኔ
ብቸኝነት ስለእኔ አጥቅቶታል
ብርድም ውርጭም ጌታዬን ጐድቶታል
4.
መልክ ውበቱን አጥቶ መድኅኔ
ጉስቁልና ቀመሰ፡ ስለእኔ
በምድር ተፈትኗል አለኝታዬ
ነፍሱን ሰጥቷል ስለእኔ ጌታዬ
100%
100%