ከፍ ከፍ በል ጌታዬ
ክበር ተመስገን ጌታዬ
የቀራንዮ ወዳጄ ባላውለታዬ
1.
የናት ውለታ ብዙ ብዙ እጅግ ብዙ ነው
ያባት ውለታ ብዙ ብዙ እጅግ ብዙ ነው
ግን ከእጅ ያጡ የነጡ ዕለት በዚያው ልክ ነው መዘዙ
አገኘሁ ተመቸኝ ወይ አጣሁ ደኸየሁ
አንድ ጊዜም ፍቅርህ ተልውጦ አላየሁ
2.
ማንም ሳያስገድድህ በፍቅር ለፍቅር ከፍቅር
ያደረክልኝ ውለታህ እንደሁ ቀራንዮ ይመስክር
ይህ አጭር ጊዜ አይበቃም አልናገር ይቅር
የምናገርበት ባይኖረኝ በቂ ቃል
ያደረግኸዉን ሁሉ ሕሊናዬ ያውቃል
3.
በፀጋህ መዳን ሳያንሰኝ መሻገር ከሞት ወደ ሕይወት
ካለም ባርነት መውጣቴ በኃይልህ የነፍሴ ነጻነት
ሥልጣን ማግኘቱ ሳይበቃ የእግዚአብሔር ልጅነት
በነፍስ በስጋዬ ማዳንህን እያየሁ
እጆችህን ይዤ ይኸው እጓዛለሁ
ተመስገን እያልኩኝ ይኸው እጓዛለሁ