ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #36h / Song #36h

መንፈስ ቅዱስ መሪያችን

Holy Spirit, Faithful Guide

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ከክርስቲያን የማይርቀው
መንፈስ ቅዱስ መሪያችን
በበረሃ ስንመንን
እጃችን ይዘህ ምራን
ስንሰማ መልካም ቃልህን
ደካሞች ደስ እንዲለን
መንፈስ ጥራኝ ና ብለህ
ስትመራኝ ልከተልህ
2.
የታመንኸው ወዳጅ ሆይ
እርዳታህ እንይይርቀን
ጨለማውም ሲያስፈራን
ጥርጥር እንዳይዘን
አውሎ ነፋስ ሲነሣ
እንዳይደክም ልባችን
መንፈስ ጥራኝ ና ብለህ
ስትመራኝ ልከተልህ
3.
የሥራ ቀን ሲያበቃ
ዕረፍታችን ስንጠብቅ
ወደ ሰማያዊ ደስታ
ለመግባት ስንናፍቅ
የየሱስ ክቡር ደሙ
ያነጻናል እንወቅ
መንፈስ ጥራኝ ና ብለህ
ስትመራኝ ልከተልህ
100%
100%