ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #8d / Song #8d

ይህ ስፍራ ጌታ ሆይ

May this place be

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: ዘማሪ እንድርያስ ሐዋዝ
👁️ Views: 30
ይህ ስፍራ ጌታ ሆይ ጌልጌላ ይሁንልን (2)
ሸለፈትን ማስወገጃ ስፍራ ጌልጌላ ይሁን ጌታ
ይህ ስፍራ ጌታ ሆይ ጵኒኤል ይሁንልን (2)
በረከትን መቀበያ ስፍራ ጵኒኤል ይሁን ጌታ
1.
ለሕዝብህ ያደረከውን ተአምራት
ያላወቀ የስምህን ብርታት
አዲስ ሸለፈታም ትውልድ በዝቶ
ሕዝብህ ይታያል በረክትን አጥቶ
ጌልጌላን ያላየ ከቶ።
2.
መቆረጥን መቆንጠጥን ጠልቶ
በጌልጌላ መሆን ክብርን ትቶ
ያልወደደ ሸለፈታም በዝቶ
ድል ከሕዝብህ ይታያል እርቆ
ጌልጌላ መሆንን ጠልቶ።
3.
ካልባረከኝ አልለቅህም ይላል
ሕዝብህ ጮሆ አደባባይ መሐል
ይህን ስፍራ ጵኒኤል አድርገው
ሹሉዳችንን በጣቶችህ ንካው
ስማችንንም ለውጠው።
100%
100%