ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #152d / Song #152d

ለውጠኝ (4) ጌታዬ

English Translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
ለውጠኝ (4) ጌታዬ
አንተን እንድትመስል አድርጋት
ኢየሱስ ሆይ ሕይወቴን
1.
እስከ መቼ ልኑር ጌታ በዚህ ሕይወት?
አንተን በማሳዘን ቁስልህን በመውጋት
መኖር አልፈልግም እያሳዘንኩ አንተን
መለወጥ እሻለሁ ፍፁም መቀየርን
2.
ሕይወቴ ይታደስ ይለወጥ ይቀየር
እኔነቴን ትቶ ክብርህን ይመስክር
በተሰበረ ልብ እንደሚለው ቃልህ
ትሁት ልሁን ጌታ ልንበርከክልህ
3.
መንፈስህ ይማርከው ሕይወቴን ይረከብ
የዓለምን ምኞት ፍፁም እንዳያስብ
ሁልጊዜ ወዳንተ ጥማት እንዲኖረኝ
ጌታ ኢየሱሴ ሆይ ለውጠኝ ለውጠኝ
4.
ብዙ ጊዜ ተጓዝኩ ርቄ ካንተ መስቀል
ኃይልን በምትሰጠኝ ባንተ ሳልታመን
ዛሬ ፈልጋለሁ እንድትለዉጠኝ
ከክብር ወደ ክብር እያሸጋገርከኝ
100%
100%