ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #72d / Song #72d

ለኔስ ጌታ ብቻ ጌታ ይሻለኛል

English translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
ለኔስ ጌታ ብቻ ጌታ ይሻለኛል
ኃዘኔን ችግሬን ይካፈልልኛል
በድካምም ኃይልን ድልን ይሰጠኛል
1.
የሎጥ ዘመን ነበር ኃጢአት የበዛበት
ሰው ዓለምን ወዶ ጌታን የካደበት
ጌታም በጣም አዝኖ እጅግም ተናዶ
ሶዶምን አጠፋ እሳቱን አውርዶ
2.
በቃሉ ብሎኛል አገሬ ሰማይ ነው
እንዴት ለዓለም ነገር ጌታን ልለውጠው
ዘመኑ ቢከፋ ብዙም ችግር ቢኖር
በጣም ይማርካል ጌታ ባንተ መኖር
3.
የሚያጽናና ወዳጅ በጎኔ ነው ጌታ
ቀጥ ብዬ ልቁም ላለም ሳልረታ
በክብሩ ስገለጥ አንድ ቀን ከሰማይ
አብሬ እሄዳለሁ ጌታን ፊቱን እንዳይ
100%
100%