እጁን ዘርግቶ ጌታ ባይረዳን ከኛ ጋር ሆኖ
በችግራችን ባይታደገን እንደዚህ ፈጥኖ
ረግረጉ ውጦን ልንጠፉ ነበር ውሃ አስጥሞን
ዛሬ ግን ድነን በሕይወት አለን ኢየሱስ አውጥቶን ።
1.
የሞትንስ ፍርድ ብዙ ጊዜ ሰምተናል
በሕይወት ለመኖር ዕለት ዕለት ሞተናል
የኢየሱስን ሞት ተሸክመን ዞረናል
በዚህ ሁሉ ግን በምህረቱ ኖረናል ።
2.
በእምነት እንጂ በምናየው አይደለም
ከጌታ በቀር እኛ ትምክህት የለንም
ጽድቃችን እንኳን ለዚህ አላበቃንም
ጸጋው አጽንቶን ከርሱ አልተለየንም ።
3.
ህያዋን ሆነን በርሱ እንኖራለን
የጌታን ሥራ ዛሬም እንገልጻለን
ክብር ለስሙ ሞገስ ለስሙ ብለን
ያለንን ሁሉ ለርሱ እንሰዋለን ።