ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #280d / Song #280d

አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ

English translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
1.
የዕውቀት ራስ የጥበብ ጌታ
ምንም ቢፈተን የማይረታ
በሰው አእምሮ አይገመትም
ወርዱም ስፋቱም አይዘልቅም
አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ
አመልካለሁ በማንም የማይረታ
አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን
አመልካለሁ የማዕዘን ዕራስን
2.
ፍቅሩን አይቼ ቀምሸዋለሁ
ፍጹም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ
በመከራዬ እርሱ እየገባ
ይጋፈጠዋል እንዳልረታ
3.
ጥፋቴን ሁሉ በፍቅር እያየ
ያሳልፈኛል ልጄ እያለ
ከሁሉም በፊት ፍቅሩ ሰብሮኛል
በመስቀሉ ላይ ነፍሱን ሰጥቶኛል
4.
ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለኝም
እንደርሱ የሚሆን ከቶ አላገኝም
የውስጥ ችግሬን ሳልነግረው ያውቃል
ለእኔ ሲከብደኝ ይሸከመዋል
100%
100%