ግዙፉ ተራራ ሜዳ ሆነልኝ
በሰላም ወጥቼ መግባት ጀምሪአለሁ
በሰላሙም አምላክ ተዳላድያለሁ
በሰላሙም አምላክ ተዳላድያለሁ
1.
ከኔ ይልቅ ላኔ ሰለምታስብልኝ
ሐዘን መከራዬ ተወገደልኝ
ያስለቀስኝ ጠላት ክግሬ በታች ወድቆአል
ልቤም በደስታ በሐሴት ተሞልቶአል
2.
ያስጨነቀኝ ሁሉ አንገት ያስደፋኝ
ሀዘን እንደ ሌለው ሰው ሀዘን የሞላኝ
በነነ ከላዬ እንደጠዋት ጤዛ
ስሙ ይባረክ አሜን ይሄው ድንቅ ጌታ
3.
አምላኩ ጥሎታል ያሉ ጠላቶቼ
ይስሙ ቀና ብዬ መቆሜን በእግሮቼ
የረዳኝ እርሱ ነው ሞገስ የሆነኝ
ጉባኤው በሙሉ አክብሩል
4.
ልዩ ነው አምላኬ ለእኔ ያስገረመኝ
ከሆንኩለት በላይ ሆኖ አስደነቀኝ
አይገርምም ወይ ሰዎች አያስደንቅም ወይ
ምስኪኑን አንስቶ ሲያቆም ከፍታ ላይ