1.
አባታችን ጌታችን ሆይ
የምትኖር በሰማይ
መንግሥትህ ትምጣልን ከላይ
ክብርህን እንድናይ
ክብርህን እንድናይ
2.
ፈቃድህ በሰማይ ቀድሞ ሕይወት እንደሆነች
እንዲሁም በምድር ደግሞ
ሰላምህን ስጠነ ሰላምህን ስጠነ
3.
ስጠነ ለሕዝብህ ዛሬ የዕለት ሲሣያችን
በደላችንንም ሁሉ
ይቅር እንድትለን ይቅር እንድትለን
4.
ጌታ ሆይ አታግባን አሁን ከክፉ ፈተና
አምላክ አንተ ካልረዳኸን
ኃይል የለንምና ኃይል የለንምና
5.
ኃይልና ምስጋና ክብርም መንግሥትም ያንተ ናት
አሜን እስከ ዘለዓለም ይሁንልን ዕረፍት
ይሁንልን ዕረፍት