ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #65h / Song #65h

ፈቃድህን አድርግ

Have Thine Own Way, Lord

ምድብ / Category: ጸሎት / Prayer
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ፈቃድህን አድርግ
ኦ ጌታ ሆይ
አንተ ሠሪ ነህ እኔ ሸክላ
አብጀኝ ሥራኝ እንደምትወድ
ስጠብቅህ ሳል በፈቃዴ
2.
ፈቃድህን አድርግ ኦ ጌታ ሆይ
መርምረኝ እየኝ ጌታ ዛሬ
እንደ በረዶ አንጻኝ አሁን
በፊትህ ስቀርብ ትሁት ልሁን
3.
ፈቃድህን አድርግ ኦ ጌታ ሆይ
መርምረኝ እና እርዳኝ ጌታ
ኃይልና ችሎት ያንተ ናቸው
ዳሰኝ ፈውሰኝ መድኃኒቴ
4.
ፈቃድህን አድርግ ኦ ጌታ ሆይ
መርምረኝ ግዛ ሰውነቴን በመንፈስ ሙላኝ ሁሉ እስኪያይ
አንተ መኖርህን በህይወቴ
100%
100%