1.
የጸሎት ሰዓት የደስታ ሰዓት
ከዓለም የምሸሽበት
አባቴንም የምሻበት
ምኞቴን የምነግርበት
ከመከራ እርቃለሁ
ጽናቴንም አገኛለሁ
ከፈተናም እድናለሁ
በጸሎትም እቀርባለሁ
2.
የጸሎት ሰዓት የደስታ ሰዓት
ጸሎቴ የሚሰማበት
አምላኬን የማገኝበት
ነፍሴ የምትረካበት
ወደ ዙፋኑም ከጠራኝ
ፀጋዬን ታመንም ካለኝ
ችግሬንም እጥላለሁ
እርሱንም እለምናለሁ
3.
የጸሎት ሰዓት የምወደው
መጽናናቱን ልካፈለው
የሰማይን ቤት እስካየው
ሩጫዬን እስክጨርሰው
በማይሞት ሥጋ እነሣለሁ
ዋጋዬንም እወስዳለሁ
በእልልታም እውላለሁ
ሣመሰግን እኖራለሁ