ኃይል ያለው በጉልበት ላይ ነው /2/
መንበርከክ መፀለይ ካለ
ሁሉም ነገር በእጃችን አለ
1.
ሙሴ በኮሬብ ተራራ እግዚአብሄርን ያናገረው
በደመና ውስጥ ተከብቦ ክብሩን ማየት የቻለው
አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመፆም በመፀለይ ነው
2.
ሐና ለረጅም ዓመታት በምላስ ዱላ ተመትታ
ጣውንቷ ስታስጨንቃት ሁል ጊዜ ጧትና ማታ
ለአምላኳ ነግራ አልቅሳ ሳሙኤልን ሰጣት ጌታ
3.
ኤልያስ ሦስት ዓመት ሙሉ ዝናብ እንዳይወርድ የዘጋው
በእምነት በፀሎት ኃይል ነው አመፀኛውን ሕዝብ የቀጣው
ለነገሥታትና ለአህዛብ የአምላኩን ክንድ የገለጸው
4.
በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ አድሮ ዳርዮስ ጠርቶ የጠየቀው
ዳንኤል አሳደረህ ወይ አምላክህ የምታመልከው
አዎን ድኜ አድሬአለሁ አምላኬን አከብረዋለሁ