1.
የሱስ ያውቃል ልቤ ሲጨ ነቅ
ደስታና መዝሙር ስናፍቅ
ሸክም ሲበዛ ደግሞም ስጨነቅ
ደክሞኝ ታክቶኝ ጉዞው ሲርቅ
አዎን ያውቃል ይጨነቃል
ሳዝን ልቡ ይነካል
ጊዜያቱ ሲያደክመኝ
ሌቱም ሲያታክተኝ
መድኃኒቴ ያውቃል
2.
የሱስ ያውቃል ሲጨልምብኝ
ድንጋጤ ፍርሃት ሲይዘኝ
ቀኑ ሲያበቃ ብርሃን ሲጨልም
ያውቀኛል ወይ እንዲቀርበኝ
3.
ያውቀኛል ወይ ፈተና ስወድቅ
በፈተና እንድዘልቅ
ለኃዘኔ ጥልቅ ረዳቴ ሲርቅ
በሌት እንቤ ሲጥለቀለቅ
4.
ያየኛል ወይ ስሰናበት
ከዘመድ ከእናት ካባት
ልቤ ሲቆስል በኃዘን ብዛት
ያውቃል ወይ የሰማይ አባት