1.
መድኃኒቴን አልለይም
መንገዱ እንዳይጠፋኝ
ከፊቱ ዘንድም አልርቅም
በክንዶቹ እንዲአቅፈኝ
አሁን ነፍሴ አትፈራም
የሱሴ ይመራኛል
በደስታም እታዘዛለሁ
እርሱን እከተላለሁ
2.
መድኃኒቴን አልለይም
እምነቴ እንዳይደክም
በቃሉ ያበረታኛል
ሌሎች በማይሰጡኝ ቃል
3.
መድኃኒቴን አልለይም
በሕይወቴ ጐዳና
ብደሰትም ቢከፋኝም
በችግር በመከራ
4.
መድኃኒቴን አልለይም
ዓይኖቹ እንዲመሩኝ
ወደ ዮርዳኖስ ሊያደርሰኝ
ወዲያ ማዶ ሊያሻግረኝ