1.
ጊዜ እንዳይጠፋ ትጉ አድርገኝ
ኃጢዓተኛ አይሙት ተስፋ ሣያገኝ
እንዴት ሥራ ልፍታ
ክርስቶስን ያወቅሁ
ፍቅርህን እንድነግር ትጋትን ስጠኝ
2.
ለጠፉት በጎችህ ጠባቂ አርገኝ
እነሱን በማሰብ ፈልጌ ላገኝ
ባጥር በጐዳና ባገር በባሕር
ለጠፉቱ ኃጣን
አድርገኝ መምሕር
3.
የፍቅር ምስጋና ላቅርብ ለጌታ
ስጦታንም ደግሞ ለፈጣሪዬ
ስለ ጸጋውም ሁሉ ጸሎት ላቅርብ
በሥራዬ ሁሉ እርሱን ደስላሰኝ
4.
ንጽህናን ስጠኝ ኃጢዓትን ልጥላ
ውስጡ ሰውነቴ ደግነት ይምላ
ራሴን ከመወደድ ነፃ
አድርገኝ አባት ሆይ
አሁን መንፈስህን ስጠኝ የሱስን ልምሰል