1.
የሱስን ማገልገል ዋጋ ይሰጣል
ፍጹም ደስታ ከርሱ ይገኛል
በቃሉ መታመን ታላቅ ዕረፍት ነው
ስለዚህ ና አገልግለው
የሱስን አገልግል ዕድሜህን ሁሉ
ዋጋ ታገኛለህና
በመንገድህ እንኳ ችግር ቢያገኝህ እርሱ ጋሻ ይሆንልሃል
2.
የሱስን አገልግል የሆነ ቢሆን
በሥራህ ሁሉ ታማኝ ሆነህ ቁም
በቃሉ መታመን ታላቅ ኃብት አለው
ስለዚህ ና አገልግለው
3.
ምናልባት ጨለማ ይሆንብናል
የሚፈትነን ኃዘን ይመጣል
ክቡር አዳኛችን ጠባቂያችን ነው
ስለዚህ ና አገልግለው