ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #82h / Song #82h

እንዴት ያለ ወዳጅ አለኝ

I've Found a Friend

ምድብ / Category: የክርስቲያን ኑሮ / Christian Life
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
እንዴት ያለ ወዳጅ አለኝ
አስቀድሞ ወደደኝ
በፍቅሩ ወደርሱ ሳበኝ
ወደርሱ አቀረበኝ
በፍቅሩ ገመድ አሰረኝ
ሊፈታ በማይቻል
እኔ የርሱ እርሱም የኔ
እስከ ዘላለም ድረስ
2.
እንዴት ያለ ወዳጅ አለኝ
ደሙን አፈሰሰልኝ
ሕይወቴን ብቻ አይደለም
ራሱንም ደግሞ ሰጠኝ
ለራሴ አንዳች የለኝም
የፈጣሪዬ እንጂ
ልቤ ብርታቴ ሕይወቴ
የርሱ ነው ለዘላለም
3.
እንዴት ያለ ወዳጅ አለኝ
ኃይል ሁሉ የተሰጠው
በሕይወት መንገድ ሊመራኝ
ወደ ሰማይ ሊያደርሰኝ
የዘላለም ክብር ታየኝ
እኔን ሊያደፋፍረኝ
አሁንም በትጋት ልሥራ
ለዘለዓለም እንዳርፍ
4.
እንዴት ያለ ወዳጅ አለኝ
ቸር እውነተኛ ታጋሽ
ጠቢብ መካር ፈቃር መሪ
ለሚወዱት ጋሻ ነው
ከብርቱ ወዳጄ የሱስ
ማን ሊለየኝ ይችላል
በሞት ሆነ በሕይወትም
ለዘላለም የርሱ ነኝ
100%
100%