ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #86h / Song #86h

የሱስ የልቤ ወዳጅ

Jesus, Lover of my Soul

ምድብ / Category: የክርስቲያን ኑሮ / Christian Life
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የሱስ የልቤ ወዳጅ
ወደ አንተ አስጠጋኝ
መከራ ሲመጣብኝ
ሞገዱ ሲነሣብኝ
ሸሽገኝ ልዑል አምላክ
የሕይወት ችግር እስኪያልፍ
ወደ ሰማይ አድርሰኝ
ነፍሴንም ተቀበላት
2.
ያላንተ ጥግ የለኝም
በአንተ ታምኛለሁ
ብቻዬን አትተወኝ
አጽናናኝ ተሸከመኝ
እታመንብህ አለሁ
እርዳታህን እሻለሁ
ደከማ ሰውነቴን
በፍቅርህ እኔን ጋርደኝ
3.
ባንተ ብቻ ከታመንሁ
ሁሉንም አገኛለሁ
ደግፍ የደከሙትን
ፈውስ የታመሙትን
አንተ እውነተኛ ነህ
እኔ ግን ያልነጻሁ ነኝ
በኃጢዓት የተሞላሁ
አንተ ታነጻኛለህ
4.
በፀጋ የተሞላህ
ለኃጢዓት ይቅርታ ሰጭ
ኃጢአቴን አስወግደህ
ና በንጽህና ያዘኝ
አንተ የሕይወት ምንጭ ነህ
በነጻ ልቀበልህ
በልቤ ውስጥም ፍለቅ
ለዘላለም ኑርልኝ
100%
100%