1.
የሱስ የኔ ነው
መልካም ተስፋ
መለኮታዊ ክብሩ ይስፋፋ
የሕይወት ወራሽ
ልንሆን ገዛን
በመንፈሱና በደም አጥቦን
ይህነው ታሪኬ ልዘምረው
መድኃኒቴንም ላመስግነው
ይህነው ታሪኬ ልዘምረው
መድኃኒቴንም ላመስግነው
2.
ፍጹም ተድላ ነው
ራስን መስጠት
የደስታ ራዕይ የሚገኝበት
መላክት ከሳማይ ይወርዳሉ
የፍቅሩን ጥልቀት እያወሩ
3.
ፍጹም ዕረፍት ነው
ራስን መስጠት
ጌታ ይሰጣል ደስታ በረከት
ያምላክን እጆች
ደጅ ስንጠና
በፍቅሩ ሞላን እንደገና