1.
በደስታ ቀን የመረጠኝ
አዳኜና አምላኬ ነው
ልቤን እጅግ ደስ ያሰኛል
ያረገውን እነግራለሁ
ደስታ ቀን ደስታ ቀን
የሱስ አጠበው ኃጢዓቴን
እንድጸልይ አስተማረኝ
በየቀኑም ደስ እንዲለኝ
ደስታ ቀን ደስታ ቀን
የሱስ አጠበው ኃጢዓቴን
2.
ታላቅ ሥራ ተፈጸመ
የጌታ ነኝ እርሱም የኔ
ይጠራኛል እመጣለሁ
ያምላኬ ቃል ደስ ያሰኛል
3.
አሁን ልቤ ዕረፍት አለው
ብሩክ በረከት አገኘ
ካንተ ከቶ አልለይም
በምሕረትህ እኖራለሁ