ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #139h / Song #139h

ግሩም ሰላም

Wonderful Peace

ምድብ / Category: ሰላም / Peace
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
1.
በመንፈሴ ጠልቆ
አሁን ዛሬ ማታ
ይሰማል የሚጣፍጥ ዜማ
የሰማዩ ዜማ ሣያቋርጥ ሲወርድ
ነፍሴ አያገኛትም ሞገድ
ሰላም ግሩም ሰላም
ከሰማይ ካባቴ የመጣ
መንፈሴን አርካልኝ
ለዘላለም ጌታ
በማይመዘነው ፍቅርህ
2.
አስደናቂው ንብረት
ይህ ሰላም የሰጠኝ
በልቤ ውስጥ ያኖረልኝ
ማንም ሊወስድብኝ
በማይቻል ቦታ
ዘመናት እስኪያልፉ በጌታ
3.
በደረስሁ ጊዜ
ከሰላም ከተማ
ድምፁንም ጆሮዬ ሲሰማ
ያንን ጣፋጭ ዜማ
ጻድቃን ሲዘምሩ
በሰማይ መንግሥት የሚኖሩ
4.
ከላይ የሚመጣ
ፍቅሩን ማን ያውቀዋል
ልባችን እንዴት ይደሰታል
በእግሩ ሥር ሆነን
ደስታን ስንካፈል
ሁሉን በመሰውያው ስንጥል
5.
የደከሙ ነፍሳት
ያጡ ደስታና ዕረፍት
በችግር ሲጓዙ
ቀን ከሌት
ጌታችን ውደዱት
ሳይጨልም ጊዜያችሁ
ታላቅ ሰላም እንዲሰጣችሁ
100%
100%