ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #180h / Song #180h

በራቀው ኮረብታ

The Old Rugged Cross

ምድብ / Category: መስቀል / Cross
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በራቀው ኮረብታ
መስቀል ይታየኛል
የየሱስ መከራ መስቀል
ከሁሉ ይልቅ ያ
መስቀል ደስ ይለኛል
ለዓለም ሞቱን ያሣያል
ስለዚህ ልውደደው መስቀሉን ከኃጢዓት ሁሉ ያዳነኝን እጠማጠማለሁ መስቀሉን ለዘውድም እለውጠዋለሁ
2.
ያ መስቀል ዓለሙ
በሙሉ የናቀው
የሚያስደንቅ መድኃኒት ነው
የሱስን የሰማይ
ቤቱን ያስለቀቀው
እኛ ልንድንበት ነው
3.
ያ አሮጌ መስቀል
ደሙ ያጠለቀው
እጅግ አምሮ ይታየኛል
በዚህ መስቀል የሱስ
ነው የተሰቀለው
ለዓለሙ ኃጢዓት ሲል
4.
ያን አሮጌ መስቀል
እኔ አምነዋለሁ
ስድቡንም እሸከምአለሁ
አንድ ቀን ከሰማይ
ቤቱ ይጠራኛል
ክብሩንም ያካፍለኛል
100%
100%