ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #224h / Song #224h

ስሜ ሲጠራ

When the Roll is Called up Yonder

ምድብ / Category: የሰማይ ቤት / Heavenly Home
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የጌታ መለከት ሲነፋ
ጊዜውም ሲፈጸም
የንጋት ብርሃን ይብራ ለዘላለም
የዳኑት ጻድቃን
ከዚህ ወደ ላይ ሲሰበሰቡ
ስሜ ሲጠራ እሆናለሁ ከዚያ
የኔ ስም ሲጠራ ሳለ
የኔ ስም ሲጠራ ሳለ
የኔ ስም ሲጠራ ሳለ
ስሜ ሲጠራ እገኛለሁ ከዚያ
2.
ጭጋግ በሌለው ጧት
በጌታ የሞቱ ሲነሱ
የትንሣኤውን ብርሃን ሲታደሉ
ቅዱሳን በሰማይ ቤታቸው ይሰበሰባሉ
ስሜ ሲጠራ እሆናለሁ ከዚያ
3.
ከጥዋት እስከ ማታ
በርትተን ለጌታ እንሥራ
ስለ ፍቅሩና ጥንቃቄው እናውራ
ሕይወት ከዓለም ሲያልፍ ሥራ ከምድር ሲፈጸም
ስሜ ሲጠራ እሆናለሁ ከዚያ
100%
100%